በዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራ ልዑክ የህዳሴ ግድብን ጎበኘ

የውሃ፣ መስኖና ኢኔርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ የተመራ ልዑካን ቡድን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ዛሬ ጎብኝቷል፡፡   

ልዑኩ የግድቡ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ የግንባታው በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ሁለት የታችኛው የውሃ ማስወጫ መስመሮች ከዚህ ቀደም የነበራቸው ችግሮች ተቀርፈው ተርባይኖቹ እየተገጠሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ 68 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ መግለጹ ይታወሳል።