የውጪ ጎብኚዎች የቆይታ ጊዜን ለማራዘም እየተሰራ ነው

ቱሪዝም ኢትዮጵያ ባዘጋጀው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡

አሁን ላይ ለስትራቴጂክ እቅዱ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን  በመሰብሰብ ለማፀደቅ እየተሰራ እንደሚገኝም የቱሪዝም ኢትዮጵያ  ማኔጀር ስለሺ ግርማ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ በቱሪዝም ኢትዮጵያና በዓለም ባንክ ትብብር እውን የሆነ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ጥናቱ በዋናነት የኮንፈረንስ  እና የማረፊያ /ስቶፕ ኦቨር ቱሪዝምን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

የማረፊያ ቱሪዝም ቱሪስቶች ከ24 ሰዓት ለበለጠ ጊዜ በእንድ ስፍራ እንዲቆዩ የሚያደርግ ዘዴ ነው፡፡

ጥናቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች እንዴት የቆይታ ጊዜያቸውን ማራዘም ይችላሉ? የሚለውን በሚመልስ መልኩ ጥናቱ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን በ2030 ከአፍሪካ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

,