ከማዕድን ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ግልጽነት ያለዉ አሰራር ያስፈልጋል – የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የሚገኘውን የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ግልጽነት የሰፈነበት አሰራር መኖር እንዳለበት ተጠቆመ።

ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የማዕድን ግልፀኝነት ኢኒሼቲቭ የቦርድ ጉባኤ ላይ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርካቶ ኢትዮጵያ በማዕድን ሀብት የበለፀገች ብትሆንም ሀብቱ በሚፈለገው ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተደረገ አለመሆኑ ገልጸዋል።

በመሆኑም ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ህብረሰተቡን ያሳተፈ ግልፀኝነት የሰፈነበት አሰራር መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ችግሩን ለማቃለል በእቅድ እየሰራ መሆኑንና፣ በተለይም የህብረሰተቡን ግንዛቤ በማሳደግ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋማት እና መንግስት በጋራ እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ሳሙኤል አክለው ገልጸዋል፡፡

በዓለም አቀፉ የማዕድን ግልፀኝነት ኢኒሼቲቭ የቦርድ ጉባኤ ከ52 ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን ገምግመዋል፡፡

ኢትዮጵያ አለም አቀፉ የማዕድን ግልጸኝነት ኢኒሼቲቭን የተቀላቀለችዉ በአውሮፓውያ የጊዜ አቆጣጠር በ2012 እንደነበር ይታወሳል፡፡