የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/ 2008 (ዋኢማ)- የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ፤ ትናንት የ2008 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት ሲያቀርቡ በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተሰሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል ።

በጤና፣ ድርቅን በመከላከል፣ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በሌሎች ልማቶች የተሰሩ ሥራዎችም ከዕቅድ አንጻር የሚያበረታቱ መሆናቸውን አብራርተዋል ።

በተለይ በክልሉ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለማቃለል ከ10 ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቀዋል።

መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በኩል የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም በቀጣይ መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ምክር ቤቱ በ2009 በጀትና ሌሎች ረቂቅ አዋጆች ላይም በትኩረት በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)