ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአየርላንድ ፓርላማ አባላት የልዑካን ቡድንን አነጋገሩ

አዲስ አበባ ህዳር 9/2004/ዋኢማ/ – ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአየርላንድ ፓርላማ አባላት የልዑካን ቡድንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት አየር ላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።

አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በእርዳታ ላይ የተመረኮዘ ብቻ ሳይሆን የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ የንግድ ግንኙነት ሊጠናክር እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከልዑካን ቡድኑ ጋር መክረዋል።

ኢትዮጵያና አየርላንድ ያላቸውን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ በሚሸጋገርበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።

የአየርላንድ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና የንግድ የጋራ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፓት ብሪን የልዑካን ቡድኑ በቆይታው በኢትዮጵያ የሚገኙ የአየርላንድ ፕሮጀክቶችን ገንዘብ አጠቃቀም ሂደት መገምገማቸውን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቶቹም የተመደበላቸውን ገንዘብ በአግባቡ እየተጠቀሙ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ነው የተናሩት፡፡

የልዑካን ቡድኑ በምስራቅ አፍሪካ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር መወያየቱም ተገልጿል፡፡