የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ለማክበር የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2004/ዋኢማ/– በአገሪቱ ለስድስተኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በከተማ ደረጃ ለማክበር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር አስታወቀ።

በአስተዳደሩ የከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞቱማ መቃሳ ትናንት ዝግጅቱን አስመክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት ለስድስተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ በመቀሌ የሚከበረውን በአል በአዲስ አበባ ከተማ ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል።

ሴክተር መስሪያ ቤቶች በአዲስ አበባ ሲቪል ሰራተኞች፣ ወጣቶችና ሴቶች የሚሳተፉበት ሲምፖዚየም ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ርዕሶች ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በከተማዋ ከ247 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተማ በተለያዩ ቦታዎች በዓሉን ያከብራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሞቱማ አስታውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከአምስተኛ ክፍል እሰከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በህገ-መንግስቱ ላይ ግንዛቤ ለማስያዝ የሚያስችል ውይይት ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ የተገባባት ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።

የባህል የኪነ-ጥበብና ፅዳት በዓሉ በፌዴራል ደረጃ ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልፀው፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በብሔር ብሔረሰቦች አደባባበይ ትርኢት እንደሚቀርብም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

በህፃናት የሚቀርብ ትርኢትና የሥነ-ጽሑፍ ውድድር እንደሚካሄድና እስከ በዓሉ ማጠቃለያ ድረስ በየደረጃው እንደሚቀርብም አስታውቀዋል።

ዓውደ ርዕይም ከተማዋን አስተዳደር በመወከል በመቀሌ እንደሚካሄድ ጠቅሰው፤ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።

በዓሉን በመቀሌ ለማክበር የሀረሪና የሶማሌ ክልል ቡድን ህዳር 23 ቀን 2004 በከተማዋ አርፈው በማግስቱ ለበዓሉ እንደሚጓዙና ለዛም አቀባባል ለማድረግ የዝግጅቱ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉም ታህሳስ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በዓሉ የራሱ መሆኑን በመረዳት በእኔነት ስሜት ማክበር እንደሚገባው አሳስበዋል።