ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ የዘመኑ ምርጥ ባንክ በመሆን ሽልማት ማግኘቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2004/ዋኢማ/– ዳሽን ባንክ “በኢትዮጵያ የዘመኑ ምርጥ ባንክ” በመሆን ለ9ኛ ጊዜ ከለንደኑ ዘባንከር ሽልማት ማግኘቱን ተገለፀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ልኡልሰገድ ተፈሪ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤  ባንኩ ሽልማቱን ያገኘው በሚሰጠው የባንክ አገልገልግሎት፣ በደንበኞች አያያዝና በዘመናዊ የባንክ አሰራሩ ነው።  

በውድድሩ 179 ባንኮች ከመላው ዓለም ተወዳድረው እንደነበር ገልፀው፤ ከተወዳደሩት ውስጥ 147 በምርጥ ባንክነት ተመርጠዋል።

ከተመረጡት ውስጥም የዳሽን ባንክ ከኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ የአመቱ ምርጥ ባንክ በመባል መሸለሙን ተናግረዋል።

የዳሽን ባንኩ ከተቋቋመ 16 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ጠቁመው፤ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እንዳቀደ ገልፀዋል።

ባንኩ በአሁኑ ወቅት 1 ቢሊየን 150 ሚሊየን የሚገመት የካፒታል በጀት እንዳለው ገልፀው፤ ባለፈው ዓመት 11 ቢሊየን ብር የነበረውን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ ወደ 14 ቢሊየን ብር ማድረሱን ተናግረዋል።

ባንኩ ስራውን ሲጀምር በ10 ቅርንጫፎች እንደነበረ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ 860ሺ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉትም ገልፀዋል።

ባንኩ ስራውን ሲጀምር 10 ቅርንጫፎች የነበሩት ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት 2ሺ 700 ቋሚና ጊዜየያዊ ሰራተኞች እንዳሉት ፕሬዚዳንቱ መግለፃቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።