ሀዋሳ፤ ታህሳስ 27 2004 /ዋኢማ/ – የሲዳማ ልማት ማህበር በ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ተቋማትን አስገንብቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን አስታወቀ፡፡
የልማት ማህበሩ ሥራስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሐንካራ ለዋልታ እንዳስታወቁት የልማት ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት ማህበሩ በሚያካሂደው በተቀናጀ የሕብረተሰብ አቀፍ ልማት ፕሮግራም አማካኝነት ነው፡፡
ሰሞኑን ለአገልግሎት የበቁት የልማት ተቋማት ስምንት የንጹህ መጠጥ ውሃ መስጫዎች፣ አንድ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ አንድ ጤና ኬላ ፣ አንድ የእንስሳት ክሊኒክና አንድ ድልድይ ናቸው፡፡
የልማት ተቋማቱ ከአራት ሺ በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ የዞኑን የጤና ፣ የንጹህ የመጠጥ ውሃና የትምህርት አቅርቦት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችሉ የማህበሩ ሥራስኪያጅ አስረድተዋል፡፡
ለልማት ተቋማቱ ግንባታ ሕብረተሰቡ የአካባቢ የግንባታ ግበዓቶችን በማቅረብና በጉልበት ሥራ ከመሳተፉ በተጨማሪ አንድ ለጋሽ ድርጅትም በገንዘብ መደገፉን ሥራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡