የኢትዮ-ጣሊያን የኢንቬስትመንት ፎረም ከየካቲት 28-29ኘ 2004 በጨጣሊያን ሮም ከተማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2004 (ዋኢማ) – የውጭ ቀጥተኛ ኢንቬስትመንትን ለማበረታታት የሚያስችል የንግድና ኢንቬስትመንት ፎረም ከየካቲት 28-29/2004 ዓ.ም እንደሚካሄድ ዋፋ ማርኬትንግና ፕሮሞሽን አስታወቀ፡፡

ፎረሙ አገሪቱ ያቀደችውን የአምስቱን ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እውን ለማድረግ አጋዥ መሆኑንም  ዋፋ ማርኬትንግና ፕሮሞሽን ኋ. የ. የግል ማህበር አስታውቋል፡፡

በዚሁ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዋፋ ማርኬትንግና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ፎረም የጣሊያን ባለሃብቶች፣ የሁለቱ አገሮች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከ60 በላይ የተለያዩ በወጪና በገቢ ንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ስኬታማ ባለሃብቶች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዋፋ ማርኬትንግና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፋንታየ ጌታሁንን ከዚህ ቀደም በአሜሪካ በእንግሊዝ እና በህንድ የተካሄዱት የኢንቬስትመንት ፎረሞች መልካም ውጤትን ያስገኙ በመሆናቸው የአገሪቱን ያልተነኩ የእንቬስትመንት ዘርፎችን ለውጥ ባለሃብቶች በማስተዋወቅ መንግስትም በዘርፉ ለሚሳተፉ ኢንቬስተሮች የተለያዩ ማበረታቻዎችን እንደሚያደርግ መግለጻቸውን  መግለጫው ጠቁሟል፡፡

በዚህ ፎረም ላይ በተላይ በእንዱስትሪው ዘርፍ አዳድስ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግሮች እንዲሁም የንግድ ትብብሮች እንደሚደረጉ ያስታወቁት ወ/ሮ ፋንታየ ዋፋ ማርኬትንግ እና ፕሮሞሽን አገሪቱ ያቀደችውን የቀጥተኛ ኢንቬስትመንት እድገት ለማገዝ ወደፊትም በተለያዩ አገራት በተለያዩ የንግድና ኢንቬስትመንት ፎሮሞችን በተመሳሳይ መልኩ የማዘጋጀቱን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወይዘሮ ፋንታየ ጌታሁን  መግለጻቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡