አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ

አዲስ አበባ መጋቢት 1/2004/ዋኢማ/- ክቡር አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዢ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በላከው መግለጫ፤ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት ለአውስትራሊያ መንግስት ጠቅላይ ገዢ ለሚስ ኩንቲነ ብሬስ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ጠቅላይ ገዢዋ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ጠቅሶ፤ በወቅቱ  ለተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ አድናቆታቸውን መግለፃቸውን መግለጫው ጠቁሟል።

ጠቅላይ ገዢዋ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል መሆኗን መግለፃቸውን መግለጫው አስታውሶ፤ ሀገራቸው አውስትራሊያም ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም በመግለጫው ተጠቁሟል።

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌም የሹመት ደብዳቤያቸውን  ባቀረቡበት ወቅት የሁለቱን አገር ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ የገለፁ ሲሆን፤ አውስትራሊያ  ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የልማት እንቅስቃሴ ድጋፍ እንድትሰጥም ጠይቀዋል።

አውስትራሊያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋርም አመርቂ ውይይት መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት የላከው መግለጫ ያስረዳል።
በመሆኗ የአውስትራሊያ አፍሪካ ዲፕሎማሲ  

ክቡር አምባሳደርም በበኩላቸው የሁለቱን አገር ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ በመግለፅ አውስትራሊያ ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የልማት እንቅስቃሴ ድጋፍ እንድትሰጥ ጠይቀዋል።

በወቅቱ አውስትራሊያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አመርቂ ውይይት ተካሂዷል።