የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አዲስ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መረጠ

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለስድስት ቀናት ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ ሲያካሂድ ሰንብቷል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ያካሄደውን ጥልቅ የተሃድሶ ግመገማ ተከትሎ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሙክታር ከድር እና ምክትላቸው ወይዘሮ አስቴር ማሞ ራሳቸውን ከሃላፊነት አንስተዋል።

ይህንንም ተከትሎ ማዕከላዊ ኮሚቴው አቶ ለማ መገርሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

የማዕከላዊ ኮሚቴው ውሳኔዎች ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።(ኤፍ ቢ ሲ)