ኢምባሲዎች ሰንደቅ ዓላማቸውን ዝቅ አድርገው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሐዘን እየተካፈሉ ነው

የአሜሪካ እና ኢንግሊዝ ኢምባሲዎችን ጨምሮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ አገራት ኢምባሲዎች በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በደረሰው የህይወት መጥፋት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ።

የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

በተመሳሳይ ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን የተመኘው የብሪታኒያ ኢምባሲ፥ በኢሬቻ ላይ በተፈጠረው ነገር ማዘኑን ገልጿል።

የስዊዲን እና የካናዳ ኢምባሲዎች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በደረሰው የህይወት መጥፋት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል-(ኤፍ ቢ ሲ) ።