ሚኒስትሩ የአስቸኳይ አዋጁን የሚያስፈፅመው ኮማንድ ፖስት ስራ መጀመሩን አስታወቁ

የመከላከያ ሚኒስትር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ስራው መጀመሩን አስታወቀ ።

የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያትና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ እንዳስታወቁት ፤በአዋጁ መሰረትም የኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ተሰይሟል።

በአዋጁ አፈጻፅም ዙሪያ ለፀጥታ ኃይሉ ማብራሪያ መሰጠቱን  ገልጸዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዋናነት የፀጥታ ሁኔታን ይቆጣጠራል፣ ለተቋማትና ለመሰረት ልማቶች ጥበቃ ያደርጋል፣ ሰብዓዊ መብት እንዳይጣስም ይቆጣጠራል።

ኮማንድ ፖስቱ ለሚያከናውናቸው ተግባራት ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጠይቌል  (ኢቢሲ) ።