ዋልታ የቴሌቭዥን ስርጭት ፍቃድ ተቀበለ

ማዕከሉ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ የብሮድካስት የፍቃድ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጋር የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ ስምምነት ተፈራርሞ ፍቃደድ ተቀበለ፡፡

ከዋልታ በተጨማሪ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የንግድ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ ተቀብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከቴሌቭዥን ጣቢያዎች በተጨማሪ ዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(ሉሲ ሬዲዮ)፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(አሀዱ ሬዲዮ) እና ኤዲስቴለር ትሬዲንግ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ፍቃድ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ሴት ቶፕ ቦክስን በአገር ውስጥ ለማምረት ለጣና ኮሙኒኬሽን እና በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሃይ ቴክ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡

ለሶስቱ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ባለፈው አመት ነሃሴ ወር ባለሥልጣኑ በሳተላይት የሚተላለፍ የንግድ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡