የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማጉላት የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

በአገሪቱ የሚገኙ ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማጉላት በአገሪቱ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን  ለመፍታት  ወሳኝ  መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ ኃይለማርያም  ደሳለኝ  ተናገሩ ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው ዕለት በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሠጡት ማብራሪያ እንደገለጹት ከሰባ በመቶ በላይ የአገሪቱ ህዝብን የሚሸፍነውን ወጣቱ መሆኑንና የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት እገዛል ያደርጋል ብለዋል ።

መንግሥት ከሥራዎቹ ሁሉ ልዩ ትኩረት የሚሠጠው ለወጣቶች  ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ የሚገኙ  ወጣቶች የማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን ለላሳደግ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ  እንደ ማነቆ የሚነሱት የፋይናንስ እጥረት እንደነበር  ያስታወሱት ጠቅላይሚኒስትሩ  በአሁኑ ወቅት  የፌደራልና የክልል መንግሥታት  ወጣቱን  የሥራ ፈጠራ ባለቤት እንዲሆኑና ተሳታፊነቱን  ለማሳደግ  በፌደራል ደረጃ 10  ቢሊዮን ብር  ተመድቧል ብለዋል ።  

መልካም  አስተዳደር     

የኢፌዴሪ መንግሥት  የአገሪቱ ህዝቦች ከመንግሥት የሚፈልጋቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ን በብቃትና በጥራት  የመሥጠት  ጉዳይ  ከመቼውም  ጊዜ በላይ  አስፈላጊ  የሆነበት ወቅት መሆኑን   ጠቅላይ  ሚንስትር ኃይለማርያም ለምክር ቤቱ በሠጡት ማብራሪያ ገልጸዋል ።

የመንግሥት ሥልጣንን  ከህዝብ ጥቅም  ይልጥ ለግል ጥቅም  የመዋል ሁኔታን ፈጽሞ  ለማስወገድ   ገዥው ፓርቲ ና መንግሥት  በጥልቅ ታህድሶ ጉዞው ተካቶ እየተሠራበት ሰለመሆኑ  ጠቅላይ ሚንስትሩ አመልክተዋል ።

የግብርና  ምርት  

በዘንድሮ  የመኸር ምርት ከሚገመተው በላይ  እንደሚሆን  ለምክር ቤቱ  የተናገሩት  ጠቅላይ ሚንስትሩ  የግብርና ምርቱ   ለአጠቃላይ  የኢኮኖሚ ዕድገቱ  አስተዋጽኦ ያበረክታል  ተብሎ እንደሚጠበቅ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል ።

ባለፈው  ዓመት  በመኸር የተገኘው  ምርት አነስተኛ  እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ  ውሃን ማዕከል   ተደርጉ  የሚሠራው  የመስኖ ሥራና  የዘንድሮ የተሻለ የመኸር ምርት  ያዓምናው ያካክሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ለምክርቤቱ አባላት  አስረድተዋል ።

የኢኮኖሚ ምዋቅዊ ሽግግር

በአገሪቱ ግብርናን  በማዘመን ከግብርናው   ወደ ኢንዱስትሪው በፍጥነት  በመሸጋገር  የተሻለ የምዋቅራዊ ሽግገርን  ለማምጣት   የተለያዩ ጥረቶች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅላይ ሚስንስትር ኃይለማርያም  ለምክር ቤቱ አብራርተዋል ። 

እንደ አብነት ለምዋቅራዊ ሽግግሩ  ወሳኝ ሚናን ሊጫወቱ  የሚችሉ 12  ትልልቅ  የኢንዱስትሪ  ፓርኮች  ግንባታ   በመንግሥትና በተለያዩ  የተሸለ ተሞክሮ ባላቸው አገራት  ድጋፍ  እየተካሄዱ ይገኛል ብለዋል ።

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች  የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱሰትሪዎችን   በክልሎች በማስፋፋት   በሁለተኛው  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን  የአነስተኛና  መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በገጠር አካባቢ እንዲገነቡ ጥረቶች ጠቅለዋል  ለመዋቅራዊ ሽግግሩም አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ እንደሚጠቀበቅ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ተናግረዋል ።

የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ

በህገ መንግሥቱ እንደተደነገገው  የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የአገሪቱ ህልውና ጉዳይ  እንደመሆኑ መጠን ዴሞክራሲን የማጥለቅና ምህዳሩን  የማስፋት  ጉዳይ    በመንግሥት ትኩረት  የተሠጠው  ጉዳይ ስለመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክርቤቱ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ  የአብላጫ  የምርጫ  ሥርዓትን በመከተል ለባለፉት  5 ተከታታይ ምርጫዎችን  ማካሄዷን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ  ባለፉት ሁለት  ምርጫዎች  ከኢህአዴግ ውጭ  ለሌሎች ፓርቲዎች  ድምጽ  የሠጡ አካላት  ድምጽ  ያልተወከለ  በመሆኑ ለወደፊቱ  የአብላጫ  የምርጫና  የተመጣጣኝ ውክልና የምርጫ ሥርዓትን አዳቅሎ የመጠቀም አስፈላጊነት ታይቷል ብለዋል ።

 ነገር ግን እንደዚህ አይነት  የምርጫ ሥርዓትን ለመከተል  በቀጣይ  ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር   በመወያያት  ድምዳሚ የሚደረስበት  ስለመሆኑ  ጠቅላይ  ሚኒስትሩ አመልክተዋል ።

የማንነት  ጥያቄን ስለመመለስ

በአንዳንድ አካባቢዎች የማንነት ጥያቄዎችን የሚቀርቡበት መንገድ  በራሱ   መታየት   የሚገባው መሆኑን   ለምክር ቤቱ የሚናገሩት  ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም  የማንነት ጥያቄዎች ሳይፈቱ   ቀርተው ሲንከባለሉ  መጥተው የግጭት  መንስኤ  ሆነው ታይተዋል ። ሆኖም የማንነት ጥያቄዎች ከአስተዳደር ጥያቄዎች ጋር በመቀላቀል   
ችግሮች  የተፈጠሩበትም ሁኔታ እንዳለ ተመልክቷል ።

ኢትዮጵያና የአባይ ተፋሰስ አገራት  

ኢትዮጵያ   ከአባይ  ወንዝ  ፍትሃዊ  ተጠቃሚ ለመሆኑን   ከግርጌ አገራት  ጋር  በመሆን  ስትሠራ ቆይታለች ።

በአባይ ጉዳይ ላይ በዲፕሎማሲ መንገድ  እንዲታይ   የምትፈልግ  መሆኑን  የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ  በአገር   ውስጥ  ጉዳይ  ጣልቃ  የመግባትን  ሁኔታ  በዓለም አቀፍ  መርህን በመከተል  ችግሩን  ለማረጋገጥ  ጥረት እየተደረገ ነው ።

ለአብነት  አንዳንድ የግብጽ  ተቋማት  ከአንዳንድ  ጸረ ሰላምና ሽብርተኛ ኃይሎች  ጋር በመመሳጠር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ  ተገቢ አለመሆኑ ለግብጽ  መንግሥት  የሚመለከታቸው አካላት  በሙሉ  መንግሥት  ማሳወቁን  የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እንዚህን ተግባራት  የግብጽ  መንግሥት  እንደማይቆጣጠራቸው በዲፕሎማሲም መንገድ ቢገለጽም የግብጽ መንግሥት  እጅ እንደሌለበት ህጋዊ እርምጃ  በመውሰድ  ገለልታኛ ስለመሆኑን  ማሳየት  ይጠበቅበታል ብለዋል ።

ሚዲያ   

በአገሪቱ  የሚዲያ ዘርፉ  በሚፈለገው  ደረጃ አለመገኘቱን  የገለጹት  ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም   አአገሪቱ  የተሻለ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስትራቴጂን    መቅረፅ  እስፈላጊ መሆኑን  ተናግረዋል ።  የሚዲያ  ሙያና ክህሎትን ለማሳደግ  በዘርፉ የአቅም ግንባታን ይበልጥ  ለመሥራት  ትኩረት  መሠጠቱን ተገልጿል ።  በአገሪቱ  የግል  ሚዲናዎችን  ለማስፋፋትና ህዝቡ  በሚፈለገው ሁኔታ  መረጃዎችን  ለማሰራጨት ጥረቶች ቀጥለዋል ብለዋል ።