የሚኒስቴሩ ሰራተኞች መንግስት ያደረገው የካቢኔዎች ድልድል የሚደነቅ መሆኑን ገለጹ

መንግስት ያደረገው አዲስ የካቢኔ ሚኒስትሮች ድልድል የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሰራተኞች በአድናቆት መቀበላቸውን አስታወቁ ፡፡

ሰራተኞቹ መንግስት ለህዝብ የገባው ቃል ለመፈጸምና ልማቱን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በማመን መደገፋቸውን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የህዝብና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ስለሺ ዘገዬ ዛሬ ለዋልታ በላኩት መግለጫ አመልክቷል ፡፡

በሀገራችን ሰላም፣ልማትና ዲሞክራሲ ለማስቀጠል በመንግስት እየተደረጉ ያሉ የለውጥ እርምጃዎች ብሄራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዳር ደርሰው ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበትን ዕድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል ፡፡

መንግስት በአርቆ አስተዋይነት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች የህዝቡ ይሁንታና ተሳታፊነት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፈው ዓመት የተቋቋመ አዲስ ቢሆንም ገና ከጅምሩ የሚታዩት የአሰራር ግድፈቶች ታርመው ራሱን ችሎ እንዲቆምና ወደ ትክክለኛው አሰራር ስርዓት እንዲሸጋገር ለማድረግ ከዘርፉ ተዋንያንና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል ፡፡

በኮንስትራክሽን ባለሙያዎች፣ ኩባንያዎችና መሳሪያዎች ምዘናና ብቃት ማረጋገጫ ቢሮ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ይታዩ የነበሩት የአሰራር ግድፈቶችና ቅሬታዎችን በማስወገድ እንደሚረባረቡም ገልጸዋል ፡፡

የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ለማድረግ የአሰራር ግድፈቶችን ለማረም የሚያስችል አሰራር ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል ፡፡

ለዚሁም ከአሁን በፊት የነበሩት ሰነዶችን የማጥራትና ርክክብ የማድረግ ፣የምዝገባ ስርዓቱን ክልሎች ወጥ በሆነ መንገድ እንዲተገብሩት እንደሚደረግ አመልክተዋል ፡፡

አዲስ የምዝገባ ሂደት በማከናወንም ብቃትን የመረጋገጥና የአሰራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት የመስራት ሂደትን በመከተል ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል ፡፡

ለተገልጋዮቹ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን ያመለከተው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ፤በቅርቡ ለሚያካሂደው ሀገራዊ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት፣ መገናኛ ብዙኋንና ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ አስተላልፏል ፡፡