የሕወሓት አመራሮች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመመለስ መዘጋጀታቸውን ገለፁ

የሕወሓት አመራሮች ከመልካም አስተዳደር እጥረት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገለፁ፡፡

የሕወሓት/ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባካሄዱት በጥልቅ የመታደስ እንቅስቃሴ  የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመመለስ እንደሚያስላቸው ገለፁ፡፡   

ሕወሓት ያለፉት ዓመታት የልማት ጉዞውን በጥልቀት በመፈተሽ ለመታደስ የሚያስችለውን መድረክ አካሂዷል፡፡

አመራሮቹ ህዝቡ ያልረካባቸውን የልማት ጥያቄዎችን በማድመጥ የተጣለባቸውን ህዝባዊና ድርጅታዊ ኃላፊነት ተረድተው የሚጠበቅባቸውን አፋጣኝ ልማትና መልካም አስተዳደር  ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ግምገማው እያንዳንዱ አመራር በስራ ሂደት የሚያጋጥሙትን ውስንነት በዝርዝር ያየበትና በሁሉም የልማት ዘርፎች መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑንም ከፍተኛ አመራሮቹ ገልፀዋል፡፡(ኢቢሲ)