በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውንና የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ፋይዳ ላይ የሚያተኩር ሴሚናር መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ።
ለአንድ ቀን በተካሄደው የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ሴሚናር የኢጋድ ሰባት አባል አገራትና የረዋንዳን ፣ የብሩንዲንና የታዛኒያን አገራት ተወካዮችን ጨምሮ የተገኙ ሲሆን የአገራቱን ትብብር ወደ የተሻለ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል ።
የኢትዮጵያ ሰላምና ድህንነት ተቋም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመተባባር ሴሚናሩ ያዘጋጁ ሲሆን አገራት የጋራ በሚያደርጓቸው የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይቶች በማድረግ የተሻለ የምስራቅ አፍሪካ ክፍለ አህጉርን ለመፍጠር እንደሚያስችላቸው ታምኖበታል ።
በሴሚናሩ የተለያዩ አገራት በክፍለ አህጉሪቱና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ልምዶቻቸውን በመለዋወጥ የተሻለ ትብብራቸውን ለወደፊቱ ይበልጥ እንዲያጎለብቱ የሚያግዝ ነው ተብሏል ።
በሴሚናሩ ላይ የተገኙት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ሴሚናሩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት ስትራቴጂካዊ በሆኑ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ ግልጽ የሆነ ምክክርና ተልዕኮ የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመው የፓሊሲ አማካሪዎች ከተናጠል ይልቅ በጋራ የፍለ አህጉራዊ ዓላማዎች ላይ ማተኮር ይገባቸዋል ብለዋል ።
እንደ አምባሳደር ታዬ ገለጻ በክፍለ አህጉሩ ያሉ አገራት አካባቢያዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን ማዕከል ባደረገና የአገሮቻቸውን ጥቅምና እሴቶችን በሚያስከብር መልኩ የውጭ ግንኙነታቸውን ቢያካሄዱ ጠቃሚ እንደሆነ ገልጸዋል ።
የፖሊሲ አውጪዎች ነባር ፖሊሲዎቻቸውን እንደገና በማጤን የጋራ ከሆነው የውጭ ፖሊሲ ስትራቴጂዎች ጋር መቆራኘታቸውንና የአካባቢያዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ስለመግባቱ ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አምባሳደሩ ተናግረዋል ።
ምሁራን የትኛውንም ፖሊሲ በምን መንገድ እየሠራ ነው የሚለውን ትንታኔን መሥጠት የሚችሉ ቢሆንም በመንግሥት አስተዳደር ላይ የሚገኘው አካል የትኛውንም በአገር ላይ የሚገኝ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን ያስገነዘቡት አምባሳደሩ በአጠቃላይ የአገራት ፖሊሲ ዕቅድ አውጪዎች ፖሊሲዎቹ እንዴት ነው ሥራ ማዋል የሚቻለውና በምን መልኩ ነው ተግባራዊ የሚደረገው የሚለው ላይ በቂ ትንታኔና ምርምር ማካሄድ ይገባቸዋል ብለዋል ።
አዲስ አበባ የሰላምና ደህንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተር አምባሳደር አልፍሬድ ማጃዬ በበኩላቸው የፖሊሲ ዕቅድና ምርምር ለውጭ ጉዳይ ፖሊሲና አተገባባር እንዲሁም ለዲፕሎማሲ ሥራው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።
በክፍለ አህጉሩ አገራት የዓለም ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ያስገባን ትንታኔንና ስትራቴጂን መሠረት ያደረገ ምክክር ማድረግ የፖለቲካ መሪዎች የዓለም አቀፉን ሁኔታ መሠረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት እንዲፈጥሩና ውሳኔን እንዲያስተላልፉ ተልቅ እገዛ እንደሚኖረው አምባሳደር አልፍሬድ አስረድተዋል ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ክፍሉ ሴሚናሩ እንዲሃድ ለተጫወተው ሚና ምስጋና አቅርበዋል ።
የኢትዮጵያ የሰላምና የደህንነት ጥናት ተቋም በአፍሪካ ሰላም ሰፍኖ ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥና በአህጉሪ ብልጽግና እንዲረጋጋጥ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ፣ ሙያዊ ምክሮችን በመለገስ፣ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ለአፍሪካውያን እያደረገ ይገኛል ።
(ትርጉም : በሰለሞን ተስፋዬ)