በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር የነበሩ ሰልጣኖች ወደ መጡበት እየተመለሱ ነው

በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረው ሁከት ውስጥ ተሳትፈው በማሰልጠኛ ጣቢያዎች የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ወደ መጡበት በመመለስ ላይ ናቸው።

እስካሁን ለአንድ ወር 1 ቀን በተሃድሶ ስልጠና ላይ የቆዩ 3 ሺህ 855 ተጠርጣሪዎች ተለቀዋል።

በተሃድሶ ስልጠናው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸውና ከተሰማሩበት የስራ ተፈናቅለው የቆት በህጉ መሰረት እንደሚስተናገዱ ነው የተገለጸው ፡፡

በቁጥጥር ስር ውለው የተለቀቁት ተጠርጣሪዎች በሰጡት አስተያየት በጥፋታቸው መጸጸታቸውን እና በተሃድሶ ስልጠናው ወቅት ተገቢው አያያዝ እንደተረገላቸው ገልጸዋል።

በቀጣይም ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ያገኙትን ትምህርትና ግንዛቤ ለህብረተሰቡ እንደሚያስተምሩም አስታውቀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ከአዋሽ፣ አላጌና ብር ሸለቆ ማዕከላት ነው የተሃድሶ ስልጠናውን በመውሰድ ወደ አካባቢያቸው የተመለሱት።

ኮማንድ ፖስቱ ባለፈው ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ በዛሬው ዕለት 9 ሺህ 800 ተጠርጣሪዎች ይለቀቃሉ ማለቱ ይታወሳል-(ኢብኮ)