ኮማንድ ፖስቱ አንዳንድ የሚታዩ ችግሮች የመፍታት ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ

ኮማንድ ፖስቱ አሁንም አልፎ አልፎ  የሚታዩ  ችግሮችን በዘላቂነት  ለመፍታት  የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ መወሰኑን አስታወቀ ፡፡

የመከላከያ  ሚንስትሩ  የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት  ሲራጅ ፈጌሳ  በሀገሪቱ

ለውጦች ቢኖሩም አሁንም አልፎ አልፎ  የሚታዩ  ችግሮችን በዘላቂነት  ለመፍታት  የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ መወሰኑንም አስገንዝበዋል።

ከሁሉም ክልሎች  የተውጣጡ የፀጥታ አካላት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት  የባለፉት  ሶስት ወራት  እቅድ አፈፃፀምን  መገምገሙን ጠቁመው ፤ኮማንድ ፖስቱ ህዝብን በማሳተፍ  በመስራቱ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን አረጋግጠዋል ፡፡

ይህም አገሪቱን በማረጋጋትና ወደ ቀድሞ  ሰላሟ  ለመመለስ  ህብረተሰቡን ያሳተፈ  ውጤታማ  ስራ ማከናወኑን ነው ያብራሩት  ።

ለኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ  በሚያከናውናቸው  ተግባራት ላይ በመምከርም  አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም አመልክተዋል-(ኢቢሲ) ።