የሚንስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ወጣቶች ተንቀሳቃሽ ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ መርቶታል።
ምክር ቤቱ ትናንትባካሄደው 21ኛ ስብሰባው በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የቀረበውን የ10 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፤ ወጣቶች ያላቸውን የማምረት አቅም ተጠቅመው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያግዝ ብሎታል፡፡
ምክር ቤቱ በብሔራዊ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ እና በማዕድን ሥራዎች ረቂቅ ደንብ ላይም ውሳኔ አሳልፏል።
የብሔራዊ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ ረቂቅ አዋጁንም ቁጠባ የማሰባሰብ፣ የስራ ፈጠራን፣ የተረጋጋ የፋይናንስ ስራዓትን እና ታማኝነትን የመጠበቅን የመሳሰሉ ተደጋጋፊ ግቦችን ለማሳካት ያስችላል ሲል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል፡፡
በተጨማሪም የውጭ ግንኙነት አግልግሎት ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ ላይም ምክርቤቱ ውሳኔ ያሳለፈበት ሌላው ጉዳይ ነው-(ኢዜአ) ፡፡