የክልሉ ተሃድሶ የልማት ግቦችን ለማሳካትና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ ተገለጸ

በቤኒሻንጉል ክልል እየተካሄደ  በሲቪል ሰርቪሱ ዘርፉ እየተካሄደ ያለው ጥልቅ ተሃድሶ የልማት ግቦችን ለማሳካትና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት እንደሚያግዝ  የክልሉ  የትምህርት ቢሮ  አስታወቀ ።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታዬ ለዋልታ እንደገለጹት በክልሉ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች  በኩል  የሚታየውን ክፍተት  በመሙላት  በሠራተኛው ውስጥ  የህዝብ አገልጋይነት መንፈስን ይበልጥ ለማጎልበት የተሃድሶ ንቅናቄ እየተደረገ ነው  ።        

በክልሉ  እየተካሄደ ያለው የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በመንግስት ካቢኔና በሥራ አስፈጻሚዎች ደረጃ  የተካሄደው  ጥልቅ ተሃድሶ  ቀጣይ ንቅናቄ ነው ያሉት  አቶ ሃብታሙ በሲቪል ሰርቪሱ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየትና እንዲቀረፉ  በማድረግ  የህብረተሰቡን  የአገልግሎት ጥማት ማርካት ያስፈልጋል ብለዋል ።      

በቤኒሻንጉል ክልል   የተሃድሶው  ንቅናቄ  ሁሉንም  የህብረተሰብ  ክፍሎችን  ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ በማሳተፍ ከ ዞን ጀምሮ  በወረዳዎች እየተካሄደ  መሆኑን  የጠቆሙት አቶ ሃብታሙ  በሚቀጥሉት  ቀናትም ተሃድሶው በሁሉም ቀበሌዎች ይቀጥላል ብለዋል ።    

ባለፉት  ወራት  በተካሄዱት የክልሉ ሥራ አስፈጻሚዎች የተሃድሶ ንቅናቄ  ውጤት መሠረት  የተለያዩ  የሥራ ኃላፊዎችን  የማዛወርና አንዳንድ አመራሮች  ከሥራ  ኃላፊነታቸው ዝቅ ብለው እንዲሠሩ መደረጉን  አቶ ሃብታሙ ተናግረዋል ።  

በቤኒሻንጉል  ክልል  በተሃድሶው ግምገማው ውጤት መሠረት 13 የዞንና  39  የወረዳ አመራሮች   ከኃላፊነታቸው ተነስተው  በቦታው አዲስ አመራሮች ተተክተዋል ።    

( ትርጉም:   በሰለሞን ተስፋዬ )