የአንካራ ዩኒቨርስቲ ለፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የክብር ሽልማት አበረከተላቸው

የአንካራ ዩኒቨርስቲ ዶክተር ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ  በአፍሪካና በቱርክ መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ላበረከቱት አስተዋፅኦ የክብር ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ዶክተር ኘሬዝዳንት ሙላቱ በአንካራ ዩንቨርስቲ ተገኝተው በቱርክና በአፍሪካ መካከል ስላለው ግንኙነት ገለጻ አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ተማሪዎች በስፍራው በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው  ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ያጠናክራል።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2006 እስከ 2013 በቆዩባቸው የአምባሳደርነት ዘመናት የአገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው ግንኙነቱ በትምህርት መስክም ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ የቱርክ መንግስት ባለፈው አመት በአገሪቱ የተቃጣውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ለማክሸፍ የተጠቀሙበትን ዲሞክራሲያዊ ሂደትም  አድንቀዋል።

የአንካራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኤርካን ኢቢስ የአንካራ እና የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት፣ በሳይንስ እና በባህል ፕሮግራሞች አብረው መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል-(ውጭ ጉዳይ)።