ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስኮች ሁሉ ከዛሚቢያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡
መሪዎቹ በሰላምና ጸጥታ፤ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ፤ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ መክረዋል፡፡
በውይይታቸውም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአፍሪካ የተጋረጠውን ሥራ አጥነት ፤ ህጋ ወጥ የሰዎች ዝውውር፤ በአየር ንብረት ለውጥ የተፈጠረውን ተጽእኖ፤ አሸባሪነትና አለመረጋጋት ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያና ዛምቢያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ በመሆናቸው እስከ አሁን ያለፉባቸው መንገዶች በቀጣይ በትብብር ለመስራት ተሞክሮና ስንቅ ይሆናል ብለዋል፡፡
የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ኤዱጋር ሳግዋ ሉ ንጎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በኢጋድ በኩል ለምስራቅ አፍሪካ አገራት ሰላምና ፀጥታ የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
መሪዎቹ በሁለቱ አገራት ህዝቦች ተጠቃሚነት በሰላምና ፀጥታ፤ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በሃይል ዘርፍ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል (ኢብኮ) ፡፡