በህዳሴው ግድብ የአማካሪ ድርጅቶች የመነሻ ሪፖረት ላይ አገራቱ ተወያዩ

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ  በአማካሪ ድርጅቶች የቀረበውን መነሻ ሪፖርትና ግድቡ በታችኛው የተፋሰሱ አገሮች ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ ዙሪያ በሳለፍነው ሰኞ ሶስትዮሹ የጋራ ኮሚቴ አገራት በካይሮ ውይይት አደረጉ፡፡

ውይይቱ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ባሳለፍነው ዕረቡ በግብጽ ተገናኝተው ውይይት ካደረጉ በኋላ መከናወኑ የጋራ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦችን በተግባር ለመተርጎምና በግድቡ ዙሪያ ያለውን መግባባት ለማጠናከር እንደሚያግዝ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ጠቁመዋል፡፡

ውይይቱ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ኤክስፐርቶች በተገኙበት ባሳለፍነው እሁድ ተጀምሮ ለአራት ቀናት ያህል እንደቆየና  ቢአርኤል እና አርቴሊያ የፈረንሳይ አማካሪ ድርጅቶች በቀረበው የመጀመሪያ ሪፖረት ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገሮች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ውይይት አድረገዋል፡፡

የሶስትዮሽ ኮሚቴው ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ በየአገራቱ የቀረቡት ሐሳቦች በማካትት የመጨረሻው ሪፖርት ውስጥ እንዲካተቱ አሳስበዋል፡፡

የአማካሪ ድርጅቱ የመነሻ ሪፖርት ከአገራቱ ጋር እንዴት መስራት እንዳለበት የቴክኒካል ምልከታዎችንና መነሻ ሁኔታዎችን ያካተተ ነው፡፡

አማካሪ ድርጅቶችቹ ጥናታቸውን በነሐሴ እንደሚያጠናቅቁና በምክረ ሐሳባቸውም ግድቡ በውሃ አጠቃቀም፣ የሐይድሮኤሌክትሪክ ሐብትና የድንበር ተሸጋሪ አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ግድቡ በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ሎኖረው የሚችለውን ተፅዕኖና ግምገማ እንደሚያካተቱ ተገልፃል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በ2003 ዓ.ም. እንደተጀመረና አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ 56 በመቶ እንደደረሰ የግብፁ ዴይሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡