በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ሊፈፅሙ በዝግጅት ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ ።
በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ብጥብጥና የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሶስት የባጃጅ አሽከርካሪዎች እና በመድሃኒዓለም ክፍለ ከተማ ደግሞ ለአድማ የሚያነሳሳ መልዕክት የያዘ ወረቀት ሲበትኑ የነበሩ አምስት የፀረ ሠላም ኃይሎች ናቸው የተያዙት።
ግለሰቦቹ በከተማዋ ነዎሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል።
በተጨማሪም ከሶስት ቀን በፊት በከተማዋ ላይ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የፀረ ሠላም ሀይሎች ከያዙት ቦምብ ጋር በፀጥታ ሀይሎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢሮው አስታውሷል።
በሌላ በኩል ነሃሴ 6 2009 ምሽት 1 ሰአት ከ50 በባህር ዳር ሰፈነ ሰላም ክፍለ ከተማ አካባቢ ቦምብ በመወርወር ለሁለት ሰዎች መቁሰል ምክንያት ሆነዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ አምቦ ቀበሌ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል(ኤፍ.ቢ.ሲ) ።