ሰበር ዜና;በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከተከሰተዉ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ 4 የስራ ሃላፊዎች ታገዱ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጠረዉን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር  በተደረገዉ ጥረት ሃላፊነታቸዉን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 4 የስራ ሃላፊዎች ታገዱ፡፡

የታገዱትም የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ፤ የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤የክልሉ ልዩ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ እና የክልሉ ልዩ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ሃላፊ ሲሆኑ በችግሩ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 11 የፖሊስ አባላት ጭምር መታገዳቸዉ ታዉቋል፡፡