ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች መሾማቸው ተገለጸ ።
የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል እንደተናገሩት ፥ ለሁለቱ ባንኮች አዳዲስ ፕሬዚዳንቶች ሹመት ተሠጥቷል።
አቶ ባጫ ጊኒ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል ።
አቶ ባጫ ቀደም ሲል የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉ ናቸው ።
እንዲሁም አቶ ኃይለኢየሱስ በቀለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳነት ሆነው ተሾመዋል።
አቶ ሃይለኢየሱስ የባንኩ ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ጌታሁን ናናን በመተካት ነው የልማት ባንክ ፕሬዚደንት ሆነው የተመደቡት ።
አቶ ኃይለየሱስ በቀለ የቀድሞው ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው።