ምክር ቤቱ ሦስት የፖለቲካ ድርጅቶችን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ሠረዘ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባደረገው ውይይት ከዚህ ቀደም  በምክርቤቱ በሽብርተኝነት ተሰይመው የነበሩትን ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር  ውስጥ እንዲሠረዙ አድርጓል ።

በፀረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 መሠረት በሽብርተኝነት የመሰየም ሥልጣን የተሠጠው ምክር ቤቱ ፤ በ2003  ዓም  በሽብርተኝነት  ዝርዝር ውስጥ እንዲገቡ ውሳኔ ተላልፈባቸው የነበሩት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች  ከዝርዝሩ ተሰርዘዋል ።

ከቅርብ  ጊዜ ወዲህ  ሦስቱም  ድርጅቶች  በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንቅሳቀሳለን  በማለታቸውና  የኢፌዴሪ መንግሥት  ይህን  ያመነበት  በመሆኑ ምክር ቤቱ ከሽብርተኝነት ዝርዝሩ እንዲሠረዙ አድርጓል ።

መንግሥት  ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት  መጎልበት  ካለው  ትልቅ  ፋይዳ  የተነሳ  ድርጅቶቹ ከሽብርተኝነት  ስያሜ  እንዲሻሩ  ተደርጓል  ተብሏል በውይይቱ ።