ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የፌደራልና ክልል ስራ ኃላፊዎች ተፈናቃዮችን ዛሬ ይጎበኛሉ

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የአሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጨምሮ የፈዳራልና የክልል ስራ ኃላፊዎች ከምዕራብና ምስራቅ ጉጂ እና ጌዲኦ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ዛሬ  እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡

የጌዲኦ ዞን ባህል ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ታሪኩ በየነ እንደገለጹት በዞኑ ተፈናቃዮቹ  በ77 መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡

እንደ አቶ ታሪኩ ገለጻ በፕሮግራሙ ላይ ሌሎች የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ይገኛሉ፤ ተፈናቃዮች በሚገኙበት ጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

በውይይቱ በገደብ ወረዳ ያሉትን ጨምሮ ከሌሎች የመጠለያ ጣቢያዎች የተወከሉ ተፈናቃዮች እንደሚሳተፉም ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጭምር የሚሳተፉበት በመሆኑ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመረው ጥረት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተመልክቷል፡፡ (ኢዜአ)