በባቢሌ የተከሰተው ግጭት ተፈትቶ ወደ ቀድሞው ሰላም መመለሱ ተጠቆመ

በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ተከስቶ የነበረው ግጭት ተፈትቶ ወደ ቀድሞው ሰላም መመለሱን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል፡፡

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ለዋልታ ቴሌቪዥን እንደገለጹት በሁለት ግለሰቦች መካከል የተፈጠረው ጸብ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

ግጭቱን ለማስቆም የወረዳው አስተዳደር ባደረገው ጥረት  ከሁለቱም ጎሳዎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች ጋር በመወያየት ችግሩን መፍታት እና ሰላም ማውረድ እንደተቻልም ጠቁመዋል፡፡

ግጭቱን ያስነሱ አካላትን ማንነት የመለየትና ለህግ የማቅረብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አቶ ታረቀኝ አስረድተዋል፡፡

በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡