ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላምና ወዳጅነት ስምምነትን ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች  በዛሬው ዕለት የሰላምና የወዳጅነት ስምምነትን ፈጸሙ ።

በስምምነቱ መሠረትም  ሀገራቱ የገቡበት ጦርነት በይፋ  ማብቃቱን አስታውቀዋል

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተደረሰው  የሰላምና ወዳጅነት ስምምነቶችን ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

በኢትዮጵያና ኤርትራ  መካከል ያለውና  ለጦርነት መፋጠጥን  በይፋ ማስቆም ወደ አዲስ የግንኙነትና ወዳጅነት ምዕራፍ ለመሸጋገር  መወሰናቸውን ባደርጉት ስምምነት አረጋግጠዋል ።

ሁለቱ  አገራት  በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ የፀጥታና ደህንነት ዘርፎች  ላይ በጋራና በትብብር ለመሥራትም ሁለቱ መሪዎች  መስማማታቸውን  ገልጸዋል።

አገራቱ የአየርና የየብስ ትራንስፖርትን የተቋረጠውን የመደበኛ ስልክ አገልግሎት እንዲሁም የንግድ ግንኙነታቸውን  ለማስጀመር የሚያስችል  ስምምነትም መሪዎቹ ፈርመዋል

ኢትዮጵያና ኤርትራ  መካከል  ተቋርጦ የነበረውን  ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማስጀመርና አጠናክሮ ለማስቀጠልም  እንቅስቃሴ ለማድረግ  ተስማምተዋል።

የአገራቱ መሪዎች በደረሱበት ስምምነት መሠረትም ኢትዮጵያ  በአስመራ ኢምባሲዋን የምትክፍት ስትሆን  ኤርትራም በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ አበባ ትከፍታለች ።  

ኢትዮጵያና ኤርትራ  የፈረሙትን የአልጀርስ ስምምነት መሠረት  የድንበር ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግና፥ ሁለቱ ሃገራት በቀጠናው ሰላም፣ ልማትና ትብብርን ለማምጣት በጋራ እንደሚሰሩም በስምምነታቸው ይፋ ተደርጓል።

ሁነተሉ አገራት ስምምነቶችመፈረምም በሃገራቱ  መካከል  ተፈጥሮ የነበረውን ጥላቻን በር በማቆም   ወደ የላቀ  የትብብር ምዕራፍ ይሸጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።