ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ይወያያሉ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአዲስ አበባ   ውይይት  እንደሚያደርጉ  ተገለጸ ።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በውይይታቸው ላይ የተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

ጠቅላይ ሚንስትር  ዶ/ር አብይ በኤርትራ  ጉብኝት  ማድረጋቸውንና የሁለቱ  አገራት ግንኙነት መሻሻሉን  ተከትሎ  ነው  አንቶኒዮ ጌተሬዝ ከጠቅላይ  ሚንስትር ዶክተር አብይ  ጋር  በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ የፈለጉት ።      

የኢትዮጵያ ኤርትራ  አየር መንገዶችም በረራ እንዲያደርጉና በወደቦች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  ያስታወቁ ሲሆን ፥ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉም ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አንስተዋል።

የተመድ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2ኛው የጋራ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ  ላይ ይገኛሉ ።