ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ድርጅት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲነሳ ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ውይይት  ባደረጉበት ወቅት ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ  ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ  ጥያቄ ያቀረቡት ።    

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

በስምምነታቸው ወቅትም በኤርትራ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱና በአለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ እየደረሰባት ያለው መገለል እንዲያበቃ፥ ኢትዮጵያ ትሰራለች ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።