የሱማሌ ብሔራዊ ክልል ሁሉንም 150 የህግ ታራሚዎችን መፍታቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በነፍስ ማጥፋትና በአስገድዶ መድፈር ከታሰሩ የህግ ታራሚዎች ውጭ ሁሉንም ታራሚዎች መፍታቱን አስታወቀ፡፡

 

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማኤል እንደገለፁት ክልሉ በየጊዜው የህግ ታራሚዎችን ሲለቅ ቆይቶ አሁን ላይ በእስር ቤት የነበሩ 150 እስረኞችን ለቋል፡፡

 

ከነዚህ ውስጥ 17 እስረኞች የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ኦብነግ አባላት መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

 

በእስር ላይ እንዲቀሩ የተደረጉት በአስገድዶ መድፈርና በነፍስ ማጥፋት የታሰሩ ብቻ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

 

ከዚህ በኋላ የእስረኞች ማቆያ የነበሩ እስር ቤቶችን ወደ እምነት ቦታነት ለመለወጥ ይሰራልም ብለዋል ፡፡(ኢቲቪ)