ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች  ምክርቤት  በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ፕሬስ  ድርጅትን የሥራ  አመራር ቦርድ ሰብሳቢና  አባላትን  ሹመት አፀደቀ ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት  ባካሄደው 3ኛ ዓመት  የሥራ  ዘመን  አስቸኳይ ስብሰባ  የኢትዮጵያ  ፕሬስ ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን  ለመሾም  የቀረበውን  የውሳኔ ሓሳብ መርምሮ አፀድቋል ።

ምክር ቤቱ ከምህረት ረቂቅ አዋጅ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና  ለማደራጀት  በወጣው  አዋጅ  ቁጥር  113  /1987 አንቀጽ 7 መሠረት የድርጅቱን የሥራ  አመራር  ቦርድ አባላትን ሹመት አጽድቋል ።

በተሠጠው  ሹመት መሠረትም አቶ ካሳሁን  ጎፌ የቦርድ ሰብሳቢ ፣  ወይዘሮ ጀሚላ ሺምብሩ ፣ ወይዘሮ አበበች  ሺከታ  ፣ አቶ በቀለ ሙለታ ፣ አቶ ዮናስ አስናቀ ፣ አቶ ወንድወሰን አንዱአለም ፣ አቶ ተካ  አባዲ እና  አቶ ዳንኤል ክብረት የቦርድ አባል በመሆን በምክር ቤቱ ተሹመዋል ።

ሹመት  የተሠጣቸው  የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮችም የተሠጣቸውን ኃላፊነት በተገቢ ሁኔታ  ለመወጣት  በምክርቤቱ ፊት  ቃለመሃላ ፈጽመዋል ።