በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር መርገቡ ተገለጸ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጋዶ ሚጢ ወረዳ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታና ያለመረጋጋት ችግር ረግቦ ወደ አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑን የክልሉ የፀጥታ ቢሮ አስታወቀ ።

የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ለዋልታ ቴሌቭዥን እንደገለጹት በተያዘው ሳምንት የክልሉ የፀረ-ሽምቅ ኃይል አባል ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ተከትሎ በሚጢ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች ሁከት መፍጠራቸው ይታወሳል፡፡

በወረዳው በተፈጠረው የፀጥታ ሂደት መስተጓጎልም ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን ተገልጿል ።

ሰሞኑን በአጋዶ ሚጢ ወረዳ የተከሰተውን ሁከትን ተከትሎ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ተከታታይ ውይይት በወረዳው ሙሉ በሙሉ ወደ  ሰላምናመረጋጋት መመለሱን  ኃላፊው ገልጸዋል፡፡