በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተከሰተው ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጎባ ከተማ በተከሰተ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልልፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ትላንት ማምሻ ከዋልታ ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ግጭቱ እንዳይሰፋ ከህዝብ ጋር በመሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ከቅዳሜ ጀምሮ በአካባቢው ያለመረጋጋት ሁኔታዎች እንዳሉት የገለጹት ኮሚሽነር የተፈጠረው  አለመረጋጋት ወደሌሎች አካባቢ እንዳይዛመት ከመከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ አባላትና ከህዝቡ ጋር በመተባበር የማረጋጋት ሥራ  እየሰራ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ እየተጣራ  ሲሆን  ተጨባጭ መረጃው ሲገኝ ለህብረሰተቡ የሚገለጽ መሆኑ ተገልጿል ።

 ከባሌ  በተከሰተው ግጭት  እስከትናንት ድረስ   የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለፀው ኮሚሽኑ ቁጥሩ ሊያሻቅብ እንደሚችልም አስታውቋል፡፡ 

በአካባቢው ድንጋይ የመወርወር እና ቤት የመፍረስ ሁኔታ እንደተስተዋለም ተገልጿል፡፡