የኢትዮጵያን ማሻሻያ የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ይደግፋል- ክሪስቲን ላጋርድ

የኢትዮጵያ እያካሄደች  ያለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማሻሻያዎች እንደሚደግፍ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም  አስታወቀ ።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ክሪስቲን ላጋርድ ጋር በዋሺንግተን ተወያይተዋል።

ክሪስቲን ላጋርድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ተቋሙ ኢትዮጵያ አሁን እያካሄደች ያለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማሻሻያ እንደሚደግፍ ገልጸው ውጤታማ የሆነ ውይይት እንዳካሄዱ አስተውቀዋል።

ተቋሙ ባወጠው መግለጫም በኢትዮጵያና ኤርትራ መሀከል የተፈረመውን የሰላምና የወዳጅነት መግለጫ አድንቆ፤ የሁለቱ ሀገራት የሰላም ስምምነት ከሀገራቱ አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ትልቅ ሚና አለው ሲል በመግለጫው አውጥቷል።