የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመደመር ጉዞ ከሚጠበቀው በላይ ሰኬታማ ነበር- ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአሜሪካው የመደመር ጉዞ ከሚጠበቀው በላይ ሰኬታማና ውጤት  የተመዘገበበት  መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሜሪካ ሀገር እያደረጉት ያለው የመደመር ጉዞ ከሚጠበቀው በላይ ውጤታማና ስኬታማ ሆኗል ብለዋል።

በአሜሪካ ጉዞ ቀደም ሲል በኢትዮጵያውያን መካከል የነበረውን ጥላቻ፣ መጠራጠርና አላስፈላጊ መከፋፈል የሚጠግን መሆኑን በግልጽ የታየ መሆኑን አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ለመተሳሰብ፣ ትብብር ለማድረግና በአንድነት ለመደጋገፍ  ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹ ሲሆን፥ ኢትዮጵያን ሀገራቸውን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትንም ለውጥ እንዲያመጡ በር ከፍተቷል  ብለዋል።(ምንጭ :ጠቅላይ  ሚንስትር ጽህፈትቤት)