የኤርትራና ጅቡቲ ጉዳይን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የኤርትራና የጂቡቲ ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ዝግጅነቷን ገለጸች።

ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ዝግጁነቷን የገለጸችው የኤርትራና ሶማሊያ ጉዳይ የሚከታተለው ኮሚቴ ባለፉት ጊዚያት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ጉብኝት ካደረገ በኋላ የ120 ቀናት ሪፖርቱን በትናንትናው ዕለት ለፀጥታው ምክር ቤት ባቀረበበት ውቅት ነው ተብሏል።

በዚህም ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለሁለት አሥርት አመታት የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት በቀጠናው አካባቢ ሰላም እንዲሰፍን እየተሠራ ያለውን ተግባር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ክብር ሊሰጠው እንደሚገባ የፀጥታው ምክር ቤት ገልጿል።              

በቀጠናው ምልከታውን ያካሄደው ኮሚቴው አሚሶም ከሶማሊያ ከመውጣቱ በፊት ሶማሊያ የአካባቢውን ጸጥታና ደህንነት በረሷ አቅም ለመወጣት የሚያስችላት ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለባት አመላክቷል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ተቀዳ አለሙ እንደገለጹት ላለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከላል የዘለቀውን ቅራኔ በመፍታት አዲስ ምዕራፍ ተክፍቷል።