ሰላምና ዴሞክራሲ ለማጎልበት ሴቶች ጉልህ አስተዋፅኦ ስላላቸው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማሳተፍ ይኖርበታል – ሴት ምሁራን

በሀገሪቷ ሰላም እና ዴሞክራሲ ለማጎልበት ሴቶች ጉልህ አስተዋፅኦ ስላላቸው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ማሳተፍ ይኖርበታል ሲሉ አስተያየታቸውን ለዋልታ የሰጡ ሴት ምሁራን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ብቃት ያላቸው ሴቶችን ወደ ኃላፊነት በማምጣት የልማቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚኖርበትም ተናግረዋል፡፡

ሴቶችን በሰላምና ልማት ስራዎች ማሳተፍ አሁን እየታየ ያለውን ለውጥ የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርግ የገለጹት ምሁራን በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው የሰቶች ተሳትፎ ያንሳል ብለዋል፡፡

በሀገር ደረጃ እየተከናወነ ባለው የሰላም እና ዲሞክራሲ ሂዴት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡