ለህዝቡ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የህወሓት የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል– ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ የለውጥ ጉዞ የክልሉን ህዝብ  ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገልጸዋል።

የህወሓት የለውጥ ጉዞ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ በቅርቡ የሚጀመረውን 13ኛውን የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤና ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ትላንት ማምሻውን በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።

የክልሉ ህዝብ በቅርቡ ያካሔደው ሰልፍ አርቆ አስተዋይነት የታየበትና ትክክለኛ ፍላጎቱን የገለጸበት መሆኑንም አስረድተዋል።

ህወሃት ህገ-መንግስቱንና የፌዴራል ስርዓቱን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም ሚናውን እንደሚወጣ ዶክተር ደብረጽዮን ተናግረዋል።

በኢትዮ-ኤርትራ ስምምነት ዙሪያም የሁለቱን ሃገራት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ እንዲደረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ መጠናከር ላይ ድርጅቱ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል። (ኢዜአ)