ኮሚቴው ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያዊያን ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባት እና የእርቀ ሰላም አስተባባሪ ኮሚቴ ከውጭና ሀገር ውስጥ ከተወጣጡ የሲቪክ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ብሔራዊ መግባባትን ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን ለመውሰድ ለነሐሴ 10/2010 መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

የመድረኩ ዋና ዓላማው በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ያስችል ዘንድ ሀገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር መሆኑን በሀገር ውስጥ የኮሚቴው አባላት በመኢአድ ጽህፈት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አስተባባሪው ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ አቶ ተሻለ ሰብሮ አሁን ከሚያካሂደው መድረክ ባሻገር በተለያዩ ጉዳዮች ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ሃሳቦች ያላቸውን አካላት በዕለቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ለማወያየት መድረክ ማዘጋጀቱንም አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው ለመንግስት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ልዩነትን በማስቀመጥ በሀገራዊ ጉዳዮችን ማጎልበት የሚችሉ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

አስባባሪው ኮሚቴ በመግለጫው ለዝግጅቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ላይ መንግስት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ኢዴፓ፣ ኢራፓ፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ የኦሞ ህዝቦች እና መኢአድ የኮሚቴው አባላት ናቸው፡፡