ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በ2010 ዓ.ም በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2010 ዓ.ም በውጭ ግንኙነት መስክ የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል፡፡ 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መስሪያ ቤቱ በ2010 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀዋል፡፡

በዋናው መስሪያ ቤትም ሆነ በሚስዮኖች የሚገኙ ሰራተኞች በቀጣዩ የበጀት ዓመት በተጨባጭ ተግባር በተሻለ የኃላፊነትና የአንድነት መንፈስ እንዲሰሩም ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለዋልታ የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡