መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት ያሰለጠናቸውን መኮንኖች አስመረቀ

 የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት አስመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት ለሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምረቃው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶከተር አብይ የህግ የበላይነት ለአንድ ሀገር ማህበረሰብ መጠበቅ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌን መንግስት እንደማይታገስ መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።