ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሶማሌ ክልል ከተወጣጡ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ከክልሉ መንግስት ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ሁኔታ ህብረተሰቡ ያሳየውን ትግዕስት ያደነቁ ሲሆን፥ የህግ የበላይነት፣ መቻቻልና መነጋገር ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስታውቀዋል።

በውይይቱ ተሳታፊዎች አጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድና ፍትህ እንዲሰጥ ነው ያሳሰቡት።

በቅርቡ በክልሉ በተከሰተው አለመረጋጋት በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው።

በዚህም የፌዴራል ፓሊስ እና የመከለከያ ሰራዊት አባላት የማረጋጋት ስራ ሰርተዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ ማእከላዊ ኮሚቴ ያካሄደውን ጉባዔ ተከትሎ በክልሉ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን ሶስት የኢሶህዴፓ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና አምስት የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች እንዲታገዱ ወስኗል፡፡(ኤፍ.ቢ.ሲ)