የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገር ሲገቡ ህዝቡ አቀባበል እንዲያደርግላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገር ሲገቡ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ህዝቡ ውጥቶ አቀባበል እንዲያደርግላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ፓርቲው በፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ  በቅርብ ጊዜያት በኢትዮጵያ እየመጡ ያሉ ለዉጦች ይበል የሚያሰኙ መሆኑን ገልጿል።

በጷጉሜ ወር ውስጥ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ወደ ሀገር እንደሚገቡም ፓርቲው ገልጸዋል።

አመራሮቹ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተዉ አቀባበል እንዲያደርጉላቸዉ ጥሪዉን አቅርቧል።

በተጨማሪ በመላዉ ሀገሪቱ የሚገኙ የፓርቲዉ መዋቅሮችም የአቀባበል ስነ ስርዓቱን በማስተባባር ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል።