ብአዴን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አገደ

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዳዋል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ሁለቱን ነባር አመራሮች ያገደው መስከረም ወር እስከሚካሄደው ጉባዔ ድረስ ነው።

አመራሮቹ የታገዱት ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ በፈፀሙት ችግር ነው ተብሏል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት ያደረገውን ስብሰባ ያጠናቀቀ ሲሆን መግለጫውን እንደሚያወጣም ይጠበቃል።