የብአዴን ውሳኔ ሀገሪቱ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ የሚያጠናክር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን) ያሳለፈው ውሳኔ ሀገሪቱ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ የሚያጠናክር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ድርጅቱ የሰጠውን መግለጫ በማስመልከት ዋልታ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በክልሉ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋምን ጨምሮ በጥረት ኮርፖሬት ስር ያሉ ኩባንያዎች ከድርጅቱ ባለቤትነት ወጥተው በክልሉ መንግስት እንዲተዳደሩ መወሰኑ የክልሉን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማፋጠን እንደምረዳም ተናግረዋል፡፡

 ድርጅቱ መግለጫው በክልሎች መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት ህዝብን ማሳተፍ ይገባል ማለቱ  ተቀባይነት ያለው ውሳኔ ነው ያሉት፡፡

ክልሉ የድርጅቱ አመራሮች የለውጥ ሂደት እንዲደግፍ እንዲሁም የህዝቡን ጥያቄ ከስር ከስር ለመመለስ በተሻለ ለውጥ እንደሚሰራ ማስታወቁ ጊዜው የሚጠይቀውን ውሳኔ እንዳሳለፉ ያስረዳል ብለዋል፡፡

ድርጅቱ በተለይ በጎንደር በኩል ከሱዳን በሚያዋስነው ድንበር ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከፌደራል መንግስት ጋር እንዲሰራም አስተያየት ሰጪዎቹ ጠይቀዋል፡፡